BBC News, አማርኛ - ዜና
ዜና
በአማራ ክልል የተፈናቃይ መጠለያ ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት 18 ሰዎች ሲገደሉ ከ30 በላይ ሰዎች ቆሰሉ
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ከኦሮሚያ ክልል ወለጋ ዞን የተፈናቀሉ ነዋሪዎች በተጠለሉበት 'ጃሪ ቁጥር 2' የተፈናቃዮች ካምፕ ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት "ሕጻናት እና ነፍሰ ጡር ሴቶችን ጨምሮ" 18 ሰዎች መገደላቸውን ሦስት የካምፑ ነዋሪዎች እና የሆስፒታል ምንጭ ለቢቢሲ ተናገሩ። ጉዳት የደረሰባቸው "8 ሕጻናት እና 10 ሴቶችን" ጨምሮ በአጠቃላይ 36 ሰዎች ወደ ሐይቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል መወሰዳቸውን አንድ የሆስፒታል ምንጭ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።
ኢትዮጵያ ዘመናዊ ጄቶችን መታጠቋ በቀጣናው ኃይል አሰላለፍ ላይ ምን ተጽእኖ ይኖረዋል?
ኢትዮጵያ 12 እጅግ ዘመናዊ የሆኑ ሱ-35 የጦር ጄቶችን ከሩሲያ መረከቧን አስታውቃለች። እነዚህን በአራተኛ እና በአምስተኛ ትውልድ ተዋጊ ጄቶች መካከል የሚገኙትን ዘመናዊ የጦር ጄቶች በመታጠቅ ከአፍሪካ ከአልጄሪያ ቀጥሎ ሁለተኛዋ አገር ናት። በአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ካለው የኃይል አሰላለፍ እና የሌሎች አገሮች ፍላጎት እንዲሁም ኢትዮጵያ በቀጣናው ያላትን ሚና ከፍ በማድረግ በኩል ፉክክሮች እየተደረጉ ባሉበት ጊዜ እነዚህ ተዋጊ ጄቶች ምን ዓይነት አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል?
ቀጥታ , ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራን ላይ ሊወሰዱ ስለሚችሉ ወታደራዊ አማራጮች ገለጻ ተደረገላቸው
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ላይ ሊወሰዱ የሚችሉ ወታደራዊ አማራጮችን በተመለከተ ከአሜሪካ ጦር የመካከለኛው ምሥራቅ ከፍተኛ አዛዥ ገለጻ እንደተሰጣቸው የአሜሪካ ዜና ምንጮች ዘገቡ። በአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዛ አዛዥ ብራድ ኩፐር ባልተለመደ ሁኔታ ለፕሬዝዳንቱ ገለጻ መስጠታቸው፣ ዋሽንግተን በቅርቡ ኢራን ላይ ወታደራዊ ዘመቻ ልትወስድ እንደምትችል የሚያመለክት መሆኑን ዎል ስትሪት ጆርናል እና አክሲዮስ ዘገባዎቸቻው አስነብበዋል።
ሩሲያ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል 'ታማኝ' አደራዳሪ መሆን ትችላለች? ለምንስ ማደራደር ፈለገች?
የዲፕሎማሲ ግንኙነታቸውን አቋርጠው ወደ ጦርነት ሊገቡ ይችላሉ ተብሎ የተሰጋላቸው የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ወዳጅ የሆነችው ሩሲያ ሁለቱን አገራት ለማሸማገል ፍላጎት እንዳላት በተደጋጋሚ ገልጻለች። አሁን ደግሞ የሁለቱ አገራት መሪዎች የሩሲያ-አፍሪካ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ሞስኮ ይገኛሉ። ሩሲያ ሁለቱን አገራት ለማቀራረብ የምታደርገው ጥረት ይሳካላታል? ለኢትዮጵያ ያስረከበቻቸው የጦር ጄቶች ጉዳይስ እንቅፋት ይፈጥራል?
ኢትዮጵያ ከሩሲያ የተረከበቻቸው የጦር ጄቶች ወታደራዊ አቅሟን ምን ያህል ይለውጡታል?
በጦር ኃይል ጥንካሬ ከአፍሪካ አገራት በአምስተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ጦር ሠራዊቷን በዘመናዊ መንገድ እያጠናከረች መሆኗን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በተደጋጋሚ ሲናገሩ ቆይተዋል። አሁን ደግሞ እጅግ ዘመናዊ የሆኑ በርካታ ሩሲያ ሠራሽ የጦር አውሮፕላኖችን መረከቧን አስታውቃለች። እነዚህ ሱ-35 ተዋጊ ጄቶች እና የኤስ-400 የአየር መከላከያዎች በኢትዮጵያ ወታደራዊ አቋም ላይ ምን ዓይነት ለውጥን ይፈጥራሉ?
ቢቢሲ አማርኛ በቲክቶክ
አስተማማኝ ዜና እና መረጃን ቅድሚያ ለማግኘት ቢቢሲ አማርኛን ቲክቶክ ላይ ይከተሉ
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናልን ይቀላቀሉ
የሰሜን ኢትዮጵያ ቀውስ
ህወሓት እንዴት በፍጥነት ሊያፈገፍግ ቻለ? በቀጣይስ ምን ሊፈጠር ይችላል?
በትግራይ ክልል ዳግም ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ በአስር ቀናት ውስጥ የህወሓት መሪዎች እና ታጣቂዎች ዋና ከተማዋን መቀለን ለቅቀው ሸሽተዋል። በተከታታይ ቀናትም የፌደራሉ መከላከያ ሠራዊት እና የትግራይ ሰላም ኃይሎች የክልሉን ዋና ዋና ከተሞች እና አብዛኛውን አካባቢ ተቆጣጥረዋል። ከቀደመው ጦርነት በተለየ የህወሓት ኃይሎች እንዴት በአጭር ጊዜ አብዛኛውን የክልሉን አካባቢ ለቀው ሊወጡ ቻሉ? በቀጣይስ በክልሉ ምን ሊፈጠር ይችላል?
ኤርትራ "በሌሎች ኃይሎች ተማምና በጥፋት መንገድ የምትቀጥል ከሆነ ከባድ ውጤት እንደሚኖረው" ጠ/ሚ ዐቢይ አስጠነቀቁ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ሰላም እንደምትፈልግ እና የልማት አጋር መሆን እንደምትሻ ጠቅሰው፤ ኤርትራ "በሌሎች ኃይሎች ተማምና በጥፋት መንገድ የምትቀጥል ከሆነ ግን ከባድ ውጤት እንደሚኖረው" ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰኞ ጥቅምት 9/2013 ዓ. ም. በትግርኛ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ላይ ነው ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር አጋርነት እንደምትፈልግ ተናግረው የማስጠንቀቂያ መልዕክትም ያስተላለፉት።
የትግራይ ባለአደራ አስተዳደር አምስቱ ተሿሚዎች እነማን ናቸው?
መስከረም አጋማሽ ላይ ዳግም ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ አብዛኛው የትግራይ ክልል አካባቢ በፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት እና በአጋር ኃይሉ ቁጥጥር ስር ገብቷል። ክልሉን በማረጋጋት እና መልሶ በመገንባት በምርጫ የሚመጣ አስተደዳር ቦታውን አስኪረከብ ድረስ ለስድስት ወራት የሚቆይ የባለአደራ አስተዳደር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተሹሟል። አምስት አባላት ያሉት ይህ ባለአደራ አስተዳደርን የሚመሩት እና የመቀለ ከተማ ከንቲባ እንዲሆኑ የተሰየሙት አምስቱ ሰዎች እነማን ናቸው?
ህወሓትን "ተገንጣይ" ያሉት ሩቢዮ በአዲስ አበባ የድሮን ጥቃት ተፈፅሞ እንደነበር ተናገሩ
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ላለፉት ሦስት ሳምንታት ከፌደራል መንግሥቱ እና ከአጋሮቹ ጋር እየተዋጋ የሚገኘውን ህወሓት "ተገንጣይ ቡድን" በማለት በአዲስ አበባ የድሮን ጥቃት ተፈጽሞ እንደነበር ተናገሩ። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ያለው ውጥረት እየጨመረ በመምጣቱ ያላቸውን ስጋትም ገልጸዋል።
የፌደራል መንግሥቱ በትግራይ ክልል ጦርነቱ መጠናቀቁን ገልጾ የባለአደራ አስተዳደር መመሥረቱን አስታወቀ
በትግራይ ክልል ለስድስት ወራት የሚቆይ ባለ አደራ አስተዳደር ተቋቋመ። በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተቋቋመው ይህ ባለአደራ አስተዳደር በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ነጻና ግልጽ ምርጫ በማከናወን ትግራይ የፌዴሬሽኑ አካል የምትሆንበትን ሁኔታ የማመቻቸት ኃላፊነት ተሰጥቶታል። በአስተዳደሩ ውስጥ በዋና አስፈጻሚነት ከተካተቱት መካከል የትግራይ ሰላም ኃይልን የሚመሩት ብ/ጄ ገብረ እግዚአብሔር በየነ ይገኙበታል።
ከሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ጋር በተያያዘ ባለፉት 5 ወራት አሜሪካ የወሰደቻቸው 5 እርምጃዎች
ደም አፋሳሹ የትግራይ ጦርነት በፕሪቶሪያ ስምምነት አማካኝነት እንዲገታ ከፍተኛ ሚና ከነበራቸው አካላት መካከል የአፍሪካ ኅብረት እና አሜሪካ ይጠቀሳሉ። አሜሪካ በአፍሪካ ቀንድ ዋነኛ ተጽዕኖ ፈጣሪ ከሆኑ ምዕራባውያን አገራት አንዷ ናት። የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ከሳምንታት በፊት ዳግም ሲቀሰቀስ ቀድመው መግለጫ ካወጡ አገራትም አንዷ ናት። አሜሪካ ከጦርነት መነሳት በፊት እና በኋላ የወሰደቻቸውን እርምጃዎች እንደሚከተለው ቃኝተናል።
ሶማሊላንድ በግብፅ የተመሠረተውን ጥምረት በመቃወም ከኢትዮጵያ ጎን እንደምትቆም ገለጸች
ሶማሊላንድ የኢትዮጵያን ደኅንነት አደጋ ላይ የሚጥል የትኛውንም ዓይነት ጣልቃ ገብነት እና ጥምረትን እንደምትቃወም ገለጸች። ነጻ አገርነቷን ያወጀችው ሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አብዲራህማን ሞሐመድ አብዱላሂ ከጎረቤታቸው ኢትዮጵያ ጋር ባላቸው ትብብር ከፍተኛ መተማመን እንዳላቸው ገልጸው "የኢትዮጵያን መረጋጋት እና ደኅንነት አደጋ ላይ የሚጥል የትኛውንም ጣልቃ ገብነት እንቃወማለን" ብለዋል።
'በሕይወት እንተርፋለን አላልንም' ፡ በህወሓት ቁጥጥር ስር የቆዩት የቀድሞ ባለሥልጣናት ምን ገጠማቸው?
የቀድሞ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደን ጨምሮ፣ አራት የቀድሞ ባለሥልጣናት ከኤርትራ ድንበር አቅራቢያ በህወሓት ታጣቂዎች ቁጥጥር ሥር ከነበሩበት እስር አምልጠው በኢትዮጵያ ሠራዊት እጅ ከገቡ በኋላ ወደ መቀለ መመለሳቸውን ተናግረዋል። ባለሥልጣናቱ ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት ከመጀመሩ በፊት በቀድሞ ጓዶቻቸው ከየቤታቸው ታግተው ከተወሰዱ በኋላ ያሳለፉትን እና እንዴት ሊያመልጡ እንደቻሉ ከመካከላቸው አንዱ ለቢቢሲ አጋርተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሩቢዮ ምን ተነጋገሩ?
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር በስልክ ተወያይተዋል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ፤ ንግግራቸው ከኤርትራ ጋር "እየተባባሰ የመጣውን ውጥረት" የተመለከተ መሆኑ ተገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የውይይቱን ይዘት በዝርዝር ባይገልጹም "እጅግ ፍሬያማ" መሆኑን አስታውቀዋል።
ሶማሊያ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል በተፈጠረው ውጥረት ገለልተኛ መሆኗን ገለፀች
የሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር ሐሰን ሞሐመድ አሊ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል በተፈጠረው ውጥረት አገራቸው "ገለልተኛ" መሆኗን ተናገሩ። ምክትል ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት ከቢቢሲ ሶማልኛ ጋር እሁድ ጥቅምት 1/2019 ዓ.ም. በነበራቸው ቃለ ምልልስ ወቅት ነው።"የሶማሊያ መንግሥት አቋም ሰላማዊ እና ገለልተኛ ነው" ያሉት ሚኒስትሩ ከአገራቱ ጋር ታሪካዊ፣ መልክዓ ምድራዊ እንዲሁም ሃይማኖታዊ ትስስር እንዳለ ተናግረዋል።
ወደ ትግራይ የተጓዙት የፌደራል መንግሥቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ምን አሉ?
በትግራይ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ ተቋርጦ የነበረው የአውሮፕላን በረራ በትናንትናው ዕለት ሲጀመር የፌደራል መንግሥቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ወደ መቀለ እና አዲግራት በማምራት ነዋሪዎችን ማግኘታቸውን ገልጸዋል። አቶ ጌታቸው ረዳ ከ18 ወራት በኋላ ወደ ክልሉ ዋና መዲና መመለሳቸውን ሲናገሩ፣ ዶ/ር አብርሃም በላይ ደግሞ "ሰላም የተጠማው ሕዝባችንን ጎበኘነው” ብለዋል። የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በበኩላቸው በመቀለ እና አዲግራት በነበራቸው ቆይታ "ጥልቅ የሰላም ጥማት" ማየታቸውን ገልጸዋል።
የኢንተርኔት ዳታን በመቆጠብ የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽን በቀላሉ ማንበብ ይፈልጋሉ?
የቢቢሲ አማርኛን ድረ ገጽ በቀላሉ በመክፈት ዜና እና ታሪኮችን በጽሑፍ ብቻ ያንብቡ!
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቪድዮዎች
ቪዲዮ, የኢትዮጵያ ጄቶች ለጎረቤቶቿ ስጋት ናቸው?
ኢትዮጵያ ቁጥራቸው 12 የሚደርሱ ሱ-35 ጄቶችን መታጠቋን አስታውቃለች። የጄቶቹን አቅም፣ በጎረቤት አገራት ዘንድ የሚፈጥሩትን ስሜት እንዲሁም አጠቃላይ በቀጣናው ስለሚኖራቸው ሚና ቢቢሲ የቀድሞውን የኢትዮጵያ አየር ኃይል አብራሪ እና አሠልጣኝ ካፒቴን ተሾመ ተንኮሉን አናግሯል።
ቪዲዮ, ኢትዮጵያ እና ሶማሊያን እንዳይተማመኑ የሚደርጓቸው ጉዳዮች ምንድን ናቸው?
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ግንኙነታቸው በጊዜ ሂደት የተለያየ ቅርጽ ሲይዝ ቆይቷል። አንዳንዴ በጠላትነት ሲፈራረጁ ሌላ ጊዜ ደግሞ ወዳጅ ይሆናሉ። አገራቱ በድንበር ይገባኛል ከባድ ጦርነቶችን ያደረጉ ቢሆንም፣ በትብብር የቆሙባቸው ጊዜያትም አሉ።ለመሆኑ የሁለቱን አገራት ግንኙነት የተረጋጋ እንዳይሆን የሚያደርገው ምክንያት ምንድን ነው?
ቪዲዮ, “እኛ አዲስ አገር ስለሆንን ምርጫ ለማካሄድ ዝግጁ አይደለንም”
ለጋዜጠኞች ክፍት ወዳልሆነችው ኤርትራ በቅርቡ የመጓዝ ዕድል አግኝታ የነበረችው የሮይተርስ ዘጋቢ ጁሊያን ፓራቪሲኒ አሥመራ በጣሊያን ጊዜ የተገነቡ ሕንጻዎቿን ጠብቃ ብዙም እንቅስቃሴ የማይደረግባት ሆና አግኝታታለች። የኢንተርኔት አገልግሎት ቁጥጥር የሚደረግበት እና ውስን በመሆኑ ሕዝቡ ከቀሪው ዓለም መነጠሉንም ታዝባለች። የአገሪቱ ባለሥልጣናትም ኤርትራ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጁ አይደለችም ብለዋታል።
ቪዲዮ, የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት እና ከኤርትራ ጋር ያለው ውጥረት
በአፍሪካ ቀንድ ያለውን ቀውስ የበለጠ ያወሳስባል ስለተባለው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት እስካሁን ምን እናውቃለን? ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በቀጥታ ጦርነት ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ?
ቪዲዮ, “ከትብብሩ ጀርባ ኤርትራ፣ ግብፅ እና ሱዳን አሉበት” ጃዋር መሐመድ
ሰባት የተቃዋሚ ኃይሎች የፈጠሩትን ትብብር አስመልክቶ ቢቢሲ ከፖለቲከኛው ጃዋር መሐመድ ጋር ቃለ መጠይቅ አድርጓል። በቃለ መጠይቁ ትብብሩ ሦስት ውጤቶች ሊኖሩት እንደሚችሉ ተናግረዋል። ከዚህም ባለፈ ኤርትራ፣ ግብፅ እና ሱዳን ከትበብሩ ጀርባ እንዳሉ ተናግረዋል።
ቪዲዮ, ሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤአይ) ሊያጠፋን ይችላል?
ሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) በተለያዩ ዘርፎች ላይ ውሎ ከፍተኛ ጥቅምን አስገኝቷል። በዚህም ውስብስብ ነገሮችን ከማቅለል አልፎ በርካታ ተግባራትን በቀላሉ ለመፈጸም አስችሏል። ይህ ደግሞ በተለያዩ መስኮች የሰዎችን ሥራ እየወሰደ እንደሆነ ሲገልጽ ቆይቶ አሁን ደግሞ የሰውን ልጅ ሊያጠፋ ይችላል የሚል ስጋት እየተሰማ ነው
ቪዲዮ, አነጋጋሪ የሆነው የቻይናው ፕሬዝዳንት የካይሮ ጉብኝት
የቻይናው ፕሬዝዳንት ካይሮን በጎበኙበት ወቅት ግብፅ በአባይ እና በቀይ ባሕር ላይ የምታራምዳቸውን አቋሞች የሚደግፍ የጋራ መግለጫ ሁለቱ አገራት አውጥተዋል። የዓለማችን አንዷ ኃያል አገር ቻይና ይህንን አቋም ማንጸባረቋ ለኢትዮጵያ ምን ማለት ነው?
ቪዲዮ, ግብፅ ትቀላቀለዋለች እየተባለ ያለው ቱርክ፣ ሳዑዲ እና ፓኪስታን የመሠረቱት 'የሙስሊም ኔቶ'
ቱርክ፣ ሳዑዲ አረቢያ እና ፓኪስታን 'የመካ ስምምነት'ን ከፈረሙ ከአንድ ሳምንት በላይ ሆኗቸዋል። አንዳንድ ተንታኞች አገራቱ የተፈራረሙትን የመከላከያ ስምምነት "የሱኒ ስምምነት" ወይም "የሙስሊም ኔቶ" ሲሉ ጠርተውታል። አንዳንዶች እንደ ኢራን እና እስራኤል ላሉ አገራት የተላለፈ መልዕክት አድርገው አቅርበውታል። ሌሎች ደግሞ ይህ ስምምነት አገራቱ ለደኅንነት ዋስትና በዩናይትድ ስቴትስ ላይ ያላቸውን ጥገኝነት ለመቀነስ ያላቸውን ፍላጎት የሚያንፀባርቅ ነው ይላሉ። ነገር ግን ሙሉው ስምምነት ለሕዝብ ይፋ ባለመሆኑ እየተሰሙ ያሉት መላምቶች ብቻ ናቸው።
ቢቢሲ አማርኛን በዋትስአፕ ላይ ያግኙ
አነጋጋሪ ጉዳይ
በኦሮሚያ ክልል ሽርካ ወረዳ በተፈጸመ ጥቃት ሕጻናትን ጨምሮ "ከ40 በላይ ሰዎች" መገደላቸውን የዐይን እማኞች ተናገሩ
በኦሮሚያ ክልል፣ አርሲ ዞን፣ ሽርካ ወረዳ በሳምንት ልዩነት ውስጥ በተፈጸመ አዲስ ጥቃት ቢያንስ አምስት ሕጻናትን ጨምሮ ከ40 በላይ ሰዎች መገደላቸው ሦስት የዐይን እማኞች ለቢቢሲ ተናገሩ። ትናንት ቅዳሜ ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም. በተፈጸመው ጥቃት የተገደሉ "46 ሰዎች" በአካባቢው በሚገኘው ቤተ ክርስቲያን "በአንድ ጉድጓድ" መቀበራቸውን ሁለት ነዋሪዎች፣ ቀብሩ የተፈጸመበት ቤተ ክርስቲያን እና የወረዳው የቤተ ክርስቲያን ምንጮች ገልጸዋል።
አርሲ ውስጥ ባለፉት ዓመታት በተፈፀሙ ጥቃቶች ብዙ ሰዎች የተገደሉባቸው የትኞቹ ናቸው?
በኦሮሚያ ክልል በአዲሱ አደረጃጀት በደቡብ ምሥራቅ ዞን ሥር በተካተተው የቀድሞው አርሲ ዞን በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠሩ ተደጋጋሚ ጥቃቶች ተፈፅመዋል። ከ2014 ዓ.ም. አንስቶ እየበረታ መምጣቱ በሚነገረው ሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት ለተወሰነ ጊዜ ጋብ እያለ ቀጥሏል። ከጥቃቱ ጀርባ ያለው ኃይል ማን ነው የሚለው ጥያቄ አሁንም እንቆቅልሽ ነው። ባለፉት ጥቂት ዓመታት በዚሁ አካባቢ ተፈጽመው በርካቶች የተገደሉባቸው ጥቃቶች የትኞቹ ናቸው?
"ገለልተኝነቴን ጠብቄ አገር ግንባታ ላይ ነበርኩ" ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ
በኢትዮጵያ ለረጅም ዘመናት የቆዩ እና የግጭት መንስዔ የሆኑ የተለያዩ አለመግባባቶችን በምክክር የመፍታት ሂደትን እንዲመራ የተቋቋመው የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሥራ ጊዜ አገሪቱ በግጭቶች ውስጥ እንዳለች ተጠናቋል። ኮሚሽኑ የምክክር ምክረ-ሃሳቦችን ለሕዝብ ይፋ ሳያደርግ የሥራ ጊዜው መጠናቀቁን እንዲሁም የሂደቱ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ ምን ይሆናል? የሚለውን በማንሳት ቢቢሲ ከአራት ዓመት በላይ በሥራ ላይ የቆየውን ኮሚሽን የመሩትን ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ጠይቋል።
የመንግሥት ለውጥ - የሰሜኑ ጦርነት - የፓርላማ የምሬት ንግግር - ስደት ፡ የገዱ አንዳርጋቸው የለውጡ ስምንት ዓመታት
አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከአገር ከመውጣታቸው በፊት መስከረም ማብቂያ ላይ በአዲስ ምክር ቤት የተተካው የቀድሞው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል፣ በክልል እና በፌደራል መንግሥቱ ውስጥ ከፍተኛ ባለሥልጣን ነበሩ። ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ሥልጣን የመጡበት ለውጥ ውስጥ ሚና ከነበራቸው ሰዎች መካከልም አንዱ ነበሩ፤ አሁን ግን በስደት ላይ ይገኛሉ። አቶ ገዱ ባለፉት 8 ዓመታት ያለፉባቸውን ውጣ ውረዶች በተመለከተ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
ኢትዮጵያ አዲስ ከገነባችው የወርቅ ማጣሪያ ፋብሪካ ምን ያህል ታተርፋለች?
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከሚጠቀሱ የወርቅ ማጣሪያ ፋብሪካዎች አንዱ ሊሆን ይችላል የተባለ ማጣሪያ ሥራ አስጀምራለች። ይህ ተቋም በጥሬው ወደ ሌሎች አገራት የሚላከውን የአገሪቱን ከፍተኛ መጠን ያለውን ወርቅ በማጣራት ዕሴት ጨምሮ ከፍተኛ ገቢን እንደሚያስገኝ እየተነገረ ነው። የፋብሪካው ከፍተኛ ባለድርሻ የሆነው መንግሥታዊው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) ለቢቢሲ ኒውስ ዴይ ፕሮግራም ስለ ፋብሪካው ተናግረዋል።
"ሁለት እህቶቼን አጥቻለሁ"፡ 139 ሰዎች ከሞቱበት የጂቡቲው የጀልባ አደጋ የተረፉ ኢትዮጵያውያን ምስክርነት
ከጂቡቲ ወደ የመን እየተጓዘ የነበረ ጀልባ ተገልብጦ 80 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ከአደጋው መትረፋቸውን ዓለም አቀፉ የስደኞች ተቋም (አይኦኤም) ገልጿል። ለመስከረም 29 አጥቢያ ማለትም መስከረም 28/2019 ዓ. ም. ምሽት ላይ ከጂቡቲ የወደብ ከተማ ኦባክ በስተሰሜን በምትገኘው ጉህሬ አቅራቢያ ጀልባው ተገልብጦ 139 ሰዎች ሞተዋል። ከዚህ አሰቃቂ አደጋ የተረፉ ኢትዮጵያውያን አደጋው እንዴት እንደተከሰተ እና የገጠማቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ከየፈርጁ
አጃኢብ!
እስከ ግማሽ ሚሊዮን ብር የሚወጣባቸው ግዙፍ የሽምግልና አበባዎች ፡ የአበባ አብዮት ወይስ የባህል ለውጥ?
ከጋብቻ በፊት የሚደረገው የሽምግልና ሥነ ሥርዓት ከፍተኛ ድግስ እና ገንዘብ የሚፈስበት እየሆነ መጥቷል። ከሚዘጋጀው ድል ያለ ድግስ ባሻገር በመቶ ሺዎች ብር የሚያስወጡ ቄንጠኛ ግዙፍ የአበባ ‘እቅፎች’ ደግሞ የሽምግልናው ሥርዓት አካል ሆነዋል። በተለይ የሚቀርበው የአበባ ስጦታ መነጋገሪያ ሆኗል። የሽምግልና ሥነ ሥርዓት የሰርግን ቦታ እየተካ ነው? ግዙፉ የአበባ ስጦታስ ከየት የመጣ ልማድ ነው?
የተመለሱ ጥያቄዎች
የአዲስ ዓመት አከባበር ሥርዓቶች በተለያዩ የዓለም አገራት
በዓለም ላይ ያሉ የተለያዩ አገራት ሕዝቦች አዲስ ዓመታቸውን የሚያከብሩት በተለያየ ጊዜ ነው። በርካታ የምዕራባውያን እና ከእነሱ ጋር ትስስር ያላቸው አገራት ጥር ወር ላይ አዲስ ዓመታቸውን የሚጀምሩ ሲሆን፣ አንዳንድ የእስያ አገራት ደግሞ ከዚህ የተለየ የአዲስ ዓመት አከባበር አላቸው። በተለያዩ የዓለማችን ክፍል የሚገኙ አገራት አዲስ ኣመትን እንዴት ያከብሩታል?
ቪዲዮ, ባለፓስፖርቶቹ የሰውን በሽታ የሚለዩት አይጦች, ርዝመት 1,28
ባለፓስፖርቶቹ የሰውን በሽታ የሚለዩት አይጦች
ቪዲዮ, የቦዲ ቢዩልደሮችን ልብ ቀጥ እያደረገ ያለው ነገር ምንድን ነው?, ርዝመት 1,24
የቦዲ ቢዩልደሮችን ልብ ቀጥ እያደረገ ያለው ነገር ምንድን ነው?















































































































